ስለ ጃሚ ዋን
ጃሚ ዋን መሰረቱን ዴንማርክ ላይ ያደረገ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማህበራዊ ለውጥ ለማምጣት እና እኩል ተጠቃሚናትን ለማረጋገጥ የሚሰራ ድርጅት ነው። ጃሚዋን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ እናቶች ጋር በመተባበር ለቁጠባ ቡድኖች መገልገያ የሚሆን የሞባይል መተግበሪያ ሰርቷል። የሞባይል መተግበሪያው ተጠቃሚ የሆኑ የቁጠባ ቡድኖች በየስብሰባዎች የሚያደርጉትን የገንዘብ እንቅስቃሴ በቀላሉ መዝግቦ መያዝ እና መከታተል እንዲችሉ ያደርጋል።
የበለጠ ለማዎቅ ከፈለጉ ድህረ ገፃችንን www.jamii-pay.com በመጎብኘት ተጨማሪ መረጃ ማግኝት ይችላሉ።
የጃሚ ፔይ መተግበሪያ
ምን ይሰራል?
- የቁጠባ ቡድን አላትን የቁጠባ መጠን በቀላሉ መዝግቦ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ያስቀምጣል።
- ስለያንዳንዱ ቡድን የቁጠባ ሁናቴ ለማወቅ እና ለመከታተል ያስችላል።
- የዲጂታል ዶሴ በመፍጠር የቁጠባ ቡድን አባላት ለገንዘብ ተቁዋማት ተደራሽ እንዲሆኑ ያመቻቻል።