የማህበረሰብዎን ደህንነት ይጠብቁ

በቁጠባ ማህበር ስብሰባዎች ወቅት የራስዎን እና የሌሎችን ደህንነት ይጠብቁ

የኮሮና ቫይረስ የበሽታውን ምልክቶች ሳያሳይ ወይም ህመም ሳይሰማ በሰውነት ውስጥ ሊቆይ ስለሚችል፣ እያንዳንዱ ሰው መመሪያዎቹን በመከተል ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረጉ አስፈላጊ ነው።

እጆችዎን ያፅዱ

ከስብሰባ በፊት ፣ በስብሰባው ወቅት እና በኋላ እጅዎን በሳሙና መታጠብ ወይም በአልኮል ማፅዳቶን ያረጋግጡ።

ሁለት እርምጃዎች ርቀትን ይጠብቁ

ሰላምታ በሚሰጡበት ወቅት ከመጨባበጥ፣ ከመተቃቀፍ እና ከመሳሳም ይታቀቡ። ሁለት እርምጃ በመራራቅ ደህንነቶን ይጠብቁ።

መዝገብ እና ብርን ሲይዙ ጨርወይም የእጅ ጓን ይጠቀሙ

የብር ኖቶች፣ ሳንቲሞች እና መዝገቦች ቫይረሱን አስተላላፊ ምንጮች ሊሆኑ ስለሚችሉ፣ በሚጠቀሙባቸው ወቅት ጨርቅ ወይም የእጅ ጓንት ይጠቀሙ።